ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ለቢሮ እና ለገቢ ማስገኛ እየተጠቀመባቸው የሚገኙ ህንፃዎችን ማለትም አዲስ አበባ (የቦሌ ባለ አራት ወለል ህንፃ እና አራት ኪሎ ባለ አራት ወለል ህንፃ) ባሕር ዳር (ባለ አራት ወለል ህንፃ) እና ጎንደር ባለ አንድ ወለል ህንፃ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር As Built Design እና የግንባታ ግምታዊ ዋጋ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዱን ለየብቻ በኢንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፁሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G- 03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር(አልማ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here