የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
56

በፍ/ባለመብት ፀደይ ሆቴል የሚጣል እቁብ ማህበር እና በፍርድ ባለ እዳ የትዋለ አይናለም መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ የባለእዳው ንብረት የሆነውን በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 ከልል ውስጥ የሚገኘውን  በአዋሳኙ፡- በምሥራቅ መከተ ጋሹ፣ በምዕራብ ፀጋየ ብዙየ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ  ሀብቴ ሙሉየ ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ የባለ እዳውን ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ ከሸያጩ ገንዘብ ውሰጥ ቢቻል ሙሉን ካልተቻለ ¼ ኛውን በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሞዴል 85 የሚያስይዝ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-ከላይ በአዋሳኝ የተጠቀሰውን ቤት ከአዋሽ ባንክ 2,762,299.43 (ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር ከአርባ ሶስት ሳንቲም) ያለበት መሆኑን እንድታውቁት ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርደ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here