በፍ/ባለመብት ፀደይ ሆቴል የሚጣል ዕቁብ ማህበር እና በፍ/ባለ እዳ አቶ አስረስ ታምር መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ የባለእዳው ንብረት የሆነውን በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 ከልል ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኙ በምሥራቅ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ክፍት ቦታ እንዲሁም በሰሜን መንገድ የሚያዋስነው በካርታ ቁጥር 064/013 የግምት መነሻ ዋጋ 3,922,500 (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት ብር) ሆኖ ሚያዝያ 03/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ የባለደውን ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ ከሽያጩ ገንዘብ ውሰጥ ቢቻል መሉውን ካልተቻለ ¼ ኛውን በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሞዴል 85 የሚያስይዝ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

