ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
72

በምሥራቅ ጐጃም ዞን የስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሚያስገነባው G+1 ህንጻ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ ግንባታ ከተያዘው የካፒታል በጀት ላይ የተቋረጠውን G+1 ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመወዳደር በዘርፉ የተሰማሩ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ምዝገባ ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የግንባታ ዋጋ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለቀሪ ግንባታው ስራ የዘመኑን ግብር የከፈሉ GC-6 BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮች መጫረት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚሰሩ ሥራዎችን ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢንድ ቦንድ) ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅ ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙበትን ሲፒኦ ወይም ደረሰኝ በተለየዩ ሶስት ፖስታዎች አሽገው ሶስቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ የመ/ቤቱን እና የአቅራቢውን ስምና አድራሻ በመጻፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 30 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው ላይ ለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 4 ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ31ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  12. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
  13. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲኖላ ተነባቢ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ማድረግና መጠን ለተቀመጠላቸው የሥራ ዝርዝሮች በሙሉ ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  15. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 288 01 22 /128 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሣሠቢያ፡- የጨረታ መክፈቻ ቀን የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

አድራሻችን ከደ/ማርቆስ ከተማ በ27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንገኛለን፡፡

የስናን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here