ግልጽ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
37

የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ 72/2004 መሠረት በ2018 በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር ከ1-6 የተዘረዘሩትን የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ 1ኛ.ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ አጀቡሽ ምትኩ፣ በምዕራብ ዋሲሁን አብተው፣ በሰሜን ዋሲሁን አብተው፣ በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ ቦታ ስፋቱ 130.25 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ፣ 2ኛ. ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ ማስረሻ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ካሳ በለጠ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 90 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ፣ 3ኛ. ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ፈንታየ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን የተመኝ በደቡብ ፔጥሮስ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 252 ካ/ሜትር ቅይጥ 01 ቦታ፣ 4ኛ. ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አበባና ሰብለ፣ በሰሜን ወኪል ሙሃመድ፣ በደቡብ ጀማል ኑሪያ መካከል የሚገኝ  ስፋቱ 185 ካ/ሜትር ቅይጥ 01 ቦታ፣ 5ኛ. ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ አዘነጋሽ ባየ፣ በምዕራብ አሰፋሽ ፍቅሬ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ እቴናት በለጠ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 96 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ እንዲሁም 6ኛ. ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ ቻላቸው አቅናው፣ በምዕራብ፣ በሰሜን እና በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ  ስፋቱ 1824.8 ካ/ሜትር አድሚንስትሬሽን 01 ቦታ ስለዚህ፡-

  1. የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ አይነት መደበኛ ነው፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን 11፡30 ነው፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/ጽ/ቤት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ሲፒኦ) በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለድርጅቱ 15 በመቶ ለመኖሪያ 20 በመቶ በማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  8. የግንባታ ደረጃ ለድርጅት
  9. የቦታው አገልግሎት በእያንዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
  10. ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 446 00 26 ደውለው ማግኝት ይችላሉ፡፡

የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here