የማዕከላዊ ጎንደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የእህል አቅርቦት፣ ፊኖ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት እና የዳቦ ማንኳፈፊያ አቅርቦት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚቀርቡ የእህል አቅርቦት፣ ፊኖ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት እንዲሁም የዳቦ ማንካፋፊያ አቅርቦት የማቅረቢያ ቦታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው በየወሩ እንደ ህግ ታራሚው ብዛት አቅርቦቱ ሊጨምርም ሊቀንስም የሚችል ሲሆን እንዲያቀርብ መምሪያው በሚገልፀው በየ ወሩ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ከጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ማድረግ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው የካቲት 30/2018 ዓ/ም ጀምሮ በጋዜጣ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ን አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከየካቲት 30/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 15/2018 ዓም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኘበት ሆነ ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 44 61 ወይም 09 64 79 28 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች

