የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ አቅርቦቶችን ሎት 1.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣ሎት2. የህክምና መሳሪያዎችን ፣ሎት3. የህክምና ግብአት አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ተከታታይ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች በዘርፉ የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የአቅርቦቶቹን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ለ15 ተከታታይ ቀናት ታትሞ ይቆይና በ16ኛዉ ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽጎ 3፡35 የሚከፈት ይሆናል።
- ኢንስቲትዩቱ እንደ በጀት መጠኑ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብት አለዉ።
- ተወዳዳሪዎች የዋጋ መሙያ ጨረታ ሰነዱን ብር 300 (ሶስት መቶ) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለህክምና መሳሪያዎች 50,000፣ ለህክምና ግብአቶች እና ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 30,000 መጠን ያላቸዉ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በሎት ምድብ በድምር ዋጋ ሲሆን የህክምና መሳሪያዎች እና የህክምና ግብአቶችን ግን በነጠላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን የበዓል ወይም ዝግ ከሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ኢንስትትዩቱ የሚሰበሰበው ሶስት በመቶ ዊዝሆልድ ብቻ ነዉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

