ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
54

በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ  ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም  በጀት አመት ለመ/ቤቱ  አገልግሎት የሚዉሉ  ሎት 1. የጽህፈት  መሳሪያ፣  ሎት 2. የቧንቧ ውኃ እቃ፣ ሎት 3. የኤሌክትሪክ እቃ፣  ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 5. ፈርኒቸር፣ ሎት 6. የጀኔሬተር እና ሎት 7. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን  ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች  የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው  ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ እና የሚጠገኑ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ  በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም (ሲፒኦ) ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ  ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከየካቲት 30/2018 እስከ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም መጋቢት 15/2018 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኝም በወቅቱ ለሚተላለፈዉ ሁሉ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል እቃ ዋጋ ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በነጠላ ዋጋ አሸናፊ መለየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንዳር ዞን ፍትህ  መምሪያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን መተማ ጠቅላላ  ሆስፒታል  ባለው ንብረት መጋዘን በዝርዝር ማስረከብ የሚችል፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 03 54 /058 331 01 75 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. አሸናፊው እቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንድ ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ያለበት እንዲሁም ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
  1. መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ እቃ አቅረቦት 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
  1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመተማ  ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here