ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
52

በምዕ/ጐጃም/ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. ስኳር እና ዘይት ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ ከተሞች ወደ ደምበጫ ፣ፍ/ሰላምና ቡሬ ከተማ ለማጓጓዝ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የደረቅ ጭነት ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑና የታደሰ የኦፕሬተር ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እና ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  1. የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማያያዝ የሚችሉ፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ  ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ  ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ  ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኑ ሂሳብ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በፓስታው ውስጥ ማስገባት እና ፓስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ  የሚቆይ ሲሆን እስከ 8ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት ይችላሉ ፤በ8ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀኑ በእለቱ  በ8ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  7. የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  8. አሸናፊው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፤ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ስኳር እና ዘይት ለአንድ አመት ማጓጓዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  10. ለማጓጓዝ ተጫራቹ በራሱ ስም የተዘጋጀ የማጓጓዣ ሰነድ (ዲስፓች) ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
  11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የመንገድ እና የቀረጥ ወጭዎችን መሸፈን አለበት፡፡
  13. ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 0640/1032 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች የመንገድ እና የቀረጥ ወጭዎችን መሸፈን የሚችል መሆን አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታው የመክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀንና ሰዓት የሚከፈት

ይሆናል፡፡

 

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ.

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here