የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ገጠር ፋ/የስራ ቡድን ለመስኖ አት/ፍራ/ዉሀ አጠቃቀም ቡድን አገልግሎት የሚውሉ የአቡካዶ እና የማንጎ ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግብርና መምሪያዉ የግብአት አቅርቦት እና ስርጭት ገጠ/ፋይ የስራ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህ ጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ማለት የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)፣ በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የማቅረቢያ ቦታ፣ የማቅረቢያ ጊዜ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን ነዉ፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ገዝቶ በመውሰድ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ ጽ/ቤቱ ድረስ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሠዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና መምሪያዉ የግብአት አቅርቦት እና ስርጭት የስራ ቡድን ቢሮ 16ኛዉ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በተናጠል /እያንዳንዱ እቃ/ ዝቅተኛ ዋጋ መሰረት ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 08 71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

