ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
47

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት አመት ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት2. የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ፤ነገር ግን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቶች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በቢሮው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጠ/ፍ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 02 56 65 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here