ግልጽ የሊዝ ጨረታ ማስታቂያ

0
41

የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከመ/ል/ጽ/ቤት የሊዝ ጨረታ ኮሜቴ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም አካል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የካቲት 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ ማወቅ እና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል በመሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ተ.ቁ የጨረታው አይነት የጨረታ ዙር የቦታው መገኛና ቀበሌ የቦታው ስፋት የቦታው አገልግሎት ቦታው የተሰጠው የጨረታ ኮድ
1 መደበኛ 3ኛ ዙር 01 ቀበሌ ከከተማ አስተዳደሩ ህንፃ ፊጽ ለፊጽ 285 ካ.ሜ ለድርጅት አገልግሎት 01
2 ›› ›› 01 ቀበሌ ከያፊት መድሃኒት መደብር በስተ ምዕራብ 409.5 ካ.ሜ ›› 02
3 ›› ›› 01 ቀበሌ አባሀቀየ ከመስጅዱ በስተ ደቡብ 148.5 ካ.ሜ ›› 03
4 ›› ›› 01 ቀበሌ ከተመቸ ሆቴል በስተ መሥራቅ በኩል 352 ካ.ሜ ›› 04
5 ›› ›› 01 ቀበሌ አባሀቀየ ከአብዱ እንድሪስ ቤት በስተ ምሥራቅ 237.65 ካ.ሜ ›› 05
6 ›› ›› 02 ቀበሌ ከንግድ ባንክ በስተ ጀርባ 125 ካ.ሜ ›› 06
7 ›› ›› 02 ቀበሌ አቢሲኒያ ባንክ ፊት ለፊት 54 ካ.ሜ ›› 07
8 ›› ›› 02 ቀበሌ አቢሲኒያ ባንክ ፊት ለፊት 70.18 ካ.ሜ ›› 08
9 ›› ›› 02 ቀበሌ ከእንድሪስ ወፍጮ ቤት ጎን 87.75 ካ.ሜ ››‹ 09

 

  1. የጨረታው ዙር፡- 3ኛ ዙር የ2018 ዓ.ም
  2. የጨረታው አይነት መደበኛ
  3. ቦታው ከማንኛውም ክርክር ነፃ የሆነ
  4. የቦታው ደረጃ 1ኛ
  5. ቦታው የሚፈቀደው አገልግሎት አይነት የህንፃው ከፍተኛ የግንባታ ወለል ግቢ ስፋት በንጽጽር በፐርስንት ሆኖ ቦታው ለሆቴል፣ ለምግብ አዳራሽ፣ ለመኝታ አገልግሎት የሚውል ሲሆን ከፍታውም G+4 ፎቅና ከዚያ በላይ በ70 በመቶ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል፡፡
  6. የጨረታ መነሻ ያሊዝ ዋጋ ለ 1 ካሬ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) ብቻ ነው፡፡
  7. የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ የቦታውን ዋጋ 20 በመቶ ይሆናል፡፡
  8. የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ መጀመሪያ ክፍያ ከተከፈነበት ከ2 ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኋላ ጀምሮ እስከ ሊዝ ዘመን 40 አመት (አርባ) ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ እንደተገለፀለት በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታ ዋጋ ከ20 በመቶ ያላነስ ቅድሚያ ክፍያ ወይም በቴክኒካል ፕሮፖዛል ላይ የገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም ውል ይፈፀማል፡፡ በተጠቀሰው ቀን በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ 2ተኛ የወጣ አንደኛ የወጣውን ዋጋ በመስጠት መውሰድ ከፈለገ ይሰጠዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የተጫረቱበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማብዛት የሚገኘውን ቤት 5 በመቶ ያላነሰ በኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቹ የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማድረግ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ በጽሁፍ ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሞላት ያኖርበታል፡፡ በፊደልና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  13. አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም፡፡ ገዝቶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  14. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ጊዜ ከየካቲት 30/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም ዓ.ም በአስር የስራ ቀናት ከቀኑ እስከ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  15. በሰነድ ማሳሰቢያው ሀሳብ ላይ በፊደልና በአሀዝ የተፃፈው ሥርዝ ድልዝና የሚያምታታ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  16. የጨረታው የሰነድ ሽያጭ የሚያልቅበት መጋቢት 11/2018 ዓ.ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
  17. ሰነዱን በመሬት ልማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  18. ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በማንኛወም የስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  19. ጨረታው የሚከፈተው መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ከረፋዱ በ4፡00 በመርሳ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  20. መስሪያ ቤቱ በጨረታው ካልተስማማ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 033 333 00 68 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመርሳ ከተማ አስ/ር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here