ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
51

በሰሜን ወሎ ዞን የዳዉንት ወረዳ ፍ/ቤት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ  የቢሮ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክ) ፣ ሎት 4 ተገጣጣሚ ቋሚ የቢሮ እቃ፣ ሎት 5 የህትመት ዉጤቶች ግዥ መፈጸም ፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና እንዲሁም ሎት 7 የተገጣጣሚ የቢሮ እቃዎች ጥገና ለማስጠገን ስለተፈለገ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ  የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆን አለባቸዉ፡፡
  3. ከ1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ሌሎች ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለው መስተካከሉ  ፓራፍ ይደረግ፡፡
  5. የሚቀርቡትን እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና የሞሉትን  ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በሞዴል 85 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ከፍ/ቤቱ የዳኝነት ገንዘብ ተቀባይ ባለሙያ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚውልበት 15 ተከታታይ ቀናት ውሰጥ ባሉት ዘወትር የመንግሰት የሥራ ቀናት መውሰድ  ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታዉ የሚዉለዉ ከመጋቢት 02/2018 ዓ/ም ጀምሮ ተከታታይ ለ15 ቀናት ሆኖ እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው በ16ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታዉ በሰዓቱ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 የሥራ ቀናት  ውስጥ ከውል ሰጭ መ/ቤቱ ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  11. የጨረታ መዝግያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጫርተው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  12. አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት (በሎት) ነዉ፡፡ ተጫራቹ አሽናፊነቱ ተገጾለት ዉል ከፈጸመ በኋላ በውለታው መሰረት እቃውን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ በራሱ ወጭ ከመ/ቤቱ ድረስ በማጓጓዝ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡ አሸናፊው ተጫራች ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ በግዥ ሂደቱ ላይ 20 በመቶ ከፍና ዝቅ ብሎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በዚህ ጨረታ ያልተገለጸ ጉዳዮች አግባብነት ባለው ግዥ ህግ   መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  15. ተጫራቾች በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 241 90 07፣ 033 241 91 13፣ 09 21 27 61 86 በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዳዉንት ወረዳ  ፍርድ ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here