ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
60

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለዘር የማይዉሉ ሰብሎችና እና የተለያዩ ብጣሪዎችን ለመሸጥ የበቆሎ ዘሮችን ከኢንተርፕራይዙ ባህር ዳር እና እንጅባራ ጣቢያ ወደ ተለያዩ ወረዳዎች ለሚገኙ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራት ድረስ ለማጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ወይም መከራየት እና ለብርሸለቆ የሸድ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል፤ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የመኪና ባለቤትነት ማረጋገጫ እና የመጫን ችሎታ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለግንባታ የሚጠይቀዉ የስራ ፈቃድ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ነዉ፤ የሙያ ብቃት ማስረጃና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸዉ፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ  ማስታወቂያው በጋዜጣ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርፕራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ባሕር ዳር ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  7.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን  8፡00  ይዘጋል፤ በዚሁ ቀን 8፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
  8. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  9. ያገለገሉ ጆንያዎችና ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርቡ አይገደድም፡፡
  10. ግዠዉን በተመለከተ ባህር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11.  ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12.  ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደ አስፈላጊነቱ መጠን እስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 6002 መላክ ይቻላል ወይም በስ.ቁ. 058 320 8415/09 18 01 69 35 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here