ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

የጨረታ መለያ ቁጥር 873/2018

የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ ጠረጴዛ እና ወንበር ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ግብር ተቀናሽ ሶስት በመቶ ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋና እና ቅጅ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር አያይዘው በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሲሞላ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሞላት አለበት፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ይቆያል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ከየካቲት 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ግዥ ፋይ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ መጋቢት 21 /2018 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02  መጋቢት 21/2018 ዓ.ም 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የህዝብ በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሁለት በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ እና በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ጥቃቅን ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ ውል በሚይዝበት ወቅት ማስያዝ ወይም በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት የሚሰሯቸውን ጠረጴዛ እና ወንበር ስራዎች ማንኛውንም ማቴሪያሎች ወጭ በራሱ አቅርቦ መስራት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  16. የውድድሩ ሁኔታ በሎት ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  17. የውል ማስከበሪያው ዋስትና ፀንቶ የሚቆየው ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  18. አሸናፊው ቅድመ ክፍያ መውሰድ የሚችለው፤ ለሚወስደው ቅድመ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ መያዣ ወይም ኮላተራል ማስያዝ የሚችል ሲሆን ነው፡፡
  19. ለተጨማሪ መረጃ የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 224 0724 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአገው ግምጃ /ቤ/ከተ/አስ/ገን/ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here