ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
103

በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የጎዛምን ወረዳ  ገንዘብ ጽ/ቤት ሎት 1. አንድ ብሎክ የመጀመሪያ ምርመራ ክፍል (OPD) እና ሎት 2.  አንድ ብሎክ የአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከል /FTC/ የግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ኮፒውን ከዋጋ መሙያ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ኮፒውን ከዋጋ መሙያ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢነት ሠርተፊኬት ያላቸውና  ማስረጃውን ኮፒውን ከዋጋ መሙያ ሠነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ከስራና ከተማ ልማት መምሪያ ሠርተፊኬት የተሠጣቸውና ኮፒውን ከዋጋ መሙያ ሠነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይዘት እና የስራ ዲዛይን (Bill Of Quantity) ከተዘጋጀው የመደበኛ የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር  500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋ አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በትንሽ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሲፒኦ ብሎ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈር በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰነዱን ለማስገባት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ለ15 ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ የመንግስት ስራ የበዓል ቀን  ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ በተመለከተ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 178 01 30 /058 771 14 22 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here