ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
106

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ ኤርፖርት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የዕቃው አይነት መለኪያ የጨረታ ማስከበሪያ በብር ለጨረታ የቀረበ የአንዱ ዋጋ
1 ያገለገሉ የሬንጅ በርሜሎች በቁጥር ብር 100,000  

 

ማሳሰቢያ፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር DA/ BJR 001/2018 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በማናቸውም ጊዜ የጨረታ ሰነድ የዋጋ መግለጫ ላይ የሚገለፀው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታክስ እና ሌሎች ማናቸውንም አይነት አስፈላጊ ክፍያዎችን አያካትትም፣ ማናቸውንም የቫት የታክስ እና ሌሎች አስፈላጊ ክፍያዎችን በሙሉ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፡፡
  3. ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኦርጅናል (Deposit slip) በመያዝ የጨረታ ሠነዱን ከየካቲት 30/2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 14/2018 ድረስ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00 እስክ 10፡00 ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ ኤርፖርት አስተዳደር እና ፋይናንስ ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡ በአካል ተገኝተው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ለማይችሉ ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው መሰረት ገቢ የተደረገበት ደረሰኝ እና በዚሁ ሰነድ ተራ ቁጥር 9 የተገለፁትን ሰነዶች በማያያዝ በኢ.ሜል አድራሻ BekaluEs@ethiopianairlines.com በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የጨረታ ሠነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ቀን እና ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ከየካቲት 30/2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 14/2018 ከረፋዱ 4፡00 እስክ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 8:00 እስከ 10:00 ባለው ጊዜ ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት መመልከት /መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተጠቀሰው የዕቃ አይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በቅድሚያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ለጨረታው ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው መጋቢት 15/2018 ከሰዓት 8፡00 ላይ አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት ይሆናል፡፡ የጨረታው አሸናፊም በደብዳቤ ይገለፅለታል፡: አጠቃላይ የጨረታው ውጤት ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይለጠፋል፡፡
  7. በትክክል የማይነበብ ያልታሸገ ፖስታ እንዲሁም ሥርዝ ድልዝ ያለው ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ማሰያዣ (ሲፒኦ) የሚያስገቡት ሠነድ ውስጥ ካልተካተተ ሠነዱ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. ከላይ ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃዉን የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሊገዙ በሚመጡበት ጊዜ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች
    • የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (2018 ዓ/ም) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    • ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም የታደሰ መንጃ ፈቃድ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
    • የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሠርተፊኬት ሠነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሠነዱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል፡፡ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን የጨረታ ሠነድ በሚገዙበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ለማያሟላ ማንኛውም ተጫራች ሠነድ የማንሸጥ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
  10. ተጫራቹ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት በጨረታው ለመሳተፍ የቀረበው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያስረዳ ሰነድ በሚመለከተው አካል የተመዘገበና የጸደቀ የመመስረቻ ፁሁፍ፣ ቃለ ጉባኤ እና የድርጅቱን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ዋጋ መሰረት በጨረታ ማስታወቂያው ወይም በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባይወስድ ወይም ባያነሳ እንዲሁም ክፍያ ባይፈጽም፣ (ውል በሚያስፈልግበት ጊዜ ውል ለመፈጸም ፈቃደኛ ባይሆን) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ወዲያውኑ ይሰረዛል፡፡ እንዲሁም ጨረታው በድጋሚ በሚወጣበት ወቅት የዋጋ ልዩነት ከመጣ ልዩነቱን እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
  12. ማንኛውም አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚያነሳበት ጊዜ ዕቃዎቹን መምረጥ አይችልም፡፡
  13. በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘበ (ቢድ ቦንድ) በሚቀጥሉት አምስት የሥራ ቀናት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  14. ድርጅቱ ጨረታውን በማንኛውም ግዜ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ እና ሰነድ ለመግዛት በስልክ ቁጥር 09 04 05 20 84 /09 53 97 23 93 /058 226 00 33 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ ኤርፖርት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here