ለካንሰር መንስኤነቱ የተረጋገጠው

0
47

ተመራማሪዎች ወደ ካንሰርነት በተለወጠ የሽንት ፊኛ እብጠት ውስጥ ዘጠና በመቶ የፕላስቲክ ቅንጣቶች ማግኘታቸው የችግሩን መንስኤ እንደሚያመላክት ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

በአሜሪካ ኒውዮርክ የሚገኘው ኤንዋይዩ ላንጐን ሄልዝ የህክምና ትምህርት ተቋም ተመራማሪዎች በ “ኘሮስቴት ካንሰር” እጢዎች ውስጥ ከጤናማ ህዋሳት ሁለት ነጥብ አምስት እጥፍ የሚበልጥ የኘላስቲክ ቅንጣቶችን አግኝተዋል፡፡ ይህም የካንሰር መስፋፋትን እንደሚያከፋው ነው የጠቆሙት፡፡

ተመራማሪዎቹ ጥልቅ ምርመራ እና ክትትል ካደረጉባቸው 10 ወንዶች በዘጠኙ የኘላስቲክ ቅንጣቶች ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህም በአቅራቢያው ከሚገኝ በካንሰር ካልተጠቃው የሰውነት ክፍል የበለጠ የፕላስቲክ ክመችት መገኘቱ የካንሰር መንስኤነቱን እንደሚያመላክት ነው እምነታቸውን ያሰፈሩት፡፡

የኘላስቲክ ደቂቅ ቅንጣቶቹ በእለት ተእለት ሁነት ወደ ሰውነት ሊገቡ እንደሚችሉ ጠቁመዋል ተመራማሪዎቹ፡፡

በማጠቃለያቸው ተመራማሪዎቹ “በኘሮስቴት ካንሰር” የተጠቃ እና ያልተጠቃ አካልን ናሙና ወስደው ፈትሸዋል፡፡ ከጥልቅ ምርምራቸውም ለማይክሮ ኘላስቲክ መጋለጥ ለ“ኘሮስቴት ካንሰር” እንደሚያጋልጥ ማስረጃ ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል- የኒወዮርክ ዩኒቨርስቲ የጤና ክፍል ኘሮፌሰር እና የምርምሩ መሪ ስቴሲ ሎብ፡፡

ለሁነቱ አሳሳቢነት በአሜሪካ ከስምንት ወንዶች አንዱ የኘሮስቴት በሽታ ያለበት መሆኑንም በዳራነት አስነብቧል- የድረ ገጹ መረጃ፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here