ግዙፉ የገበያ ማእከል

0
42

በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ባለ 16 ፎቅ 700 ሱቆችን የያዘው የገበያ ማእከል በግዙፍነቱ በዓለም ቀዳሚ መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

በ2009 እ.አ.አ  “ማሲ” የተሰኘን የገበያ ማእከል ከአንደኛነት መንበር ያወረደው የደቡብ ኮሪያው ሺንሳጌ ሴንተም አሁን ድረስ መሪነቱን እንደያዘ ነው፡፡ የገበያ ማእከሉ ስፋት 293,900 ካሬሜትር ተለክቷል፡፡ በዚህም በግዙፍነቱ ቀዳሚነትን ተቆናጧል፡፡

የገበያ ማእከሉ ከሱቆች በተጨማሪ የጐልፍ ስፖርት መጫዎቻ ሜዳዎች፣ የጥበብ ውጤቶች ዓውደ ርእይ ማቅረቢያ ስፍራዎች፣ የፊልም እና የቲያትር ማቅረቢያ መድረኮች እና ጽህፈት ቤቶችን ይዟል፡፡

በግዙፉ የገበያ ማእከል ውስጥ ትርኢቶችን ለሚያቀርቡ ለጽህፈት ቤቶች እና በየመዝናኛ ቤቶች ለሚያገለግሉ ሰራተኞች፣ ለእንግዶች የገላ መታጠቢያ እና መፀዳጃ ቤቶች የተገልጋዩን ብዛት ከግምት ውስጥ በማስገባት በግንባታው ተካተዋል፡፡

ግዙፉን የገበያ ማእከል ተዘዋውሮ  በአንዴ ጐብኝቶ ለመጨረስ ቀናትን እንደሚሻ ድረገፆች አስነብበዋል፡፡

በገበያ ማእከሉ በተካተቱ ሱቆች፣ የትርኢት ማቅረቢያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የጥበባት ውጤቶች ማሳያዎች ወ.ዘ.ተ ከአንድ ነጥብ 38 ቢሊዮን ዶላር በላይ የግብይት ገቢ ማስመዝገቡም በማጠቃለያነት ለንባብ በቅቷል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here