የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አማካኝነት ለውኃ ልማት ጽ/ቤት፣ ለእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መምሪያ፣ ለግብርና መምሪያ የመስኖ ካናል ግንባታ ማስገንባት እና የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የውኃ እቃ፣ ሎት 2 የእንቁላል ጣይ ደሮ፣ ሎት 3 የደሮ መኖ፣ ሎት 4 የእንስሳት መድሀኒት እንዲሁም ሎት 5 የመስኖ ካናል ግንባታ ሲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ በተጠቀሰው የጨረታ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ያቀረበው ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግለጫ (ሰፔስፊሌሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሚወዳደሩበት የዕቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ደብረ ታቦር ከተማ አስ/ገን/መምሪያ በጥሬ ገንዘብ በመሂ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ስም ፊርማ፣ ማህተም ጨረታው ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለፅ በደ/ታ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል፡፡
- በጋዜጣ የወጣው ጨረታ የሚከፈትበት እለት በዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀንና ሰዓቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከነጠላም ዋጋ ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች ላይ የሚሞላ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ (ተመስርቶ) መጫረት አይችሉም፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንደም እቃ ሳይሟላ መቅረብ የለበትም ሳያሟላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- የእቃው መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- መምሪያው በጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን ዓይነት የመግዛት መብት አለው፡፡
- እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደ/ታ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ/ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 02 09 /058 141 93 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

