በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስ/ቡድን ከ2018 የመደበኛ በጀት ለግብርና ጽ/ቤት የመስኖ ፕሮጀክት ካናል ጥገና ስራ፣ ለውሃ ጽ/ቤት የዉሃ ፓምፕ፣ እንዲሁም ለእ/አ/ህ/ል ጽ/ቤት የ3 ወር ኮኮክ ዝርያ ዶሮዎች እና የተመጣጠነ የቄብ ዶሮዎች መኖ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ጨረታ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ደብረ ኤልያስ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በዕለቱ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በጽ/ቤቱ የግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ የዉሃ ፓንፕ ብር 7000 (ሰባት ሽህ ብር) ብቻ የመስኖ ፕሮጀክት የካናል ጥገና ብር 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) ብቻ የ3 ወር ኮኮክ ዝርያ ዶሮዎች ብር 3,000 (ሶስት ሽህ ብር) ብቻ የተመጣጠነ የቄብ ዶሮዎች መኖ ብር 3,000 (ሶስት ሽህ ብር) ብቻ በጽ/ቤታችን በመሂ 1 ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- የመስኖ ካናል ግንባታ ጥገና ተጫራቾች ደረጃ WC 8 እና በላይ መሆን የሚገባቸው ሲሆን የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ በአድራሻ ለደ/ኤ/ ገንዘብ ጽ/ቤት በማድረግ የድርጅቱን ማህተም በመርገጥ ኦሪጅናል ለብቻው ኮፒውን ለብቻው አስፈላጊ ሰነዶችን በማሟላት በፖስታ በማሸግ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ብቻ ቢሮ ቁጥር 08 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ ጽ/ቤቱ በመሂ 1 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ለመስኖ ካናል ግንባታ ጥገና አሸናፊው ያሸነፈበት ዋጋ ከመሀንዲስ ግምት በታች የተጋነነ 25 በመቶ በታች ከሆነ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 25 በመቶ ጽ/ቤቱ መሂ 1 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከአሰሪው መስሪያ ቤት ጋር ውል በመያዝ ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በአድራሻ ለደብረ ኤልያስ ገንዘብ ጽ/ቤት በማድረግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻ በመሙላት የታደሰ ንግድ ፈቃድና (ቲን) ምዝገባ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት በማያያዝ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለ30 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያስቀምጠው አይነት ወይም ስፔስፊኬሽን መሰረት ሰነዳቸውን ሞልተው ማቅረብ
ይኖርባቸዋል፡፡ - ተጫራቹ የአሸነፈውን እቃ የደብረ ኤልያስ ወረዳ በሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ውድድሩ በጥቅል በዋጋ ድምር ወይም /በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ሌሎች ያልተጠቀሱ አሰራሮች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና የክልል ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ክቢ 01/02 በቀን 15/09/2014 ዓ.ም ባወጠው በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ላይ በተደረገ የማሻሻያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 058 250 04 85 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

