በአብክመ ጤና ቢሮ የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ በ2018 በጀት አመት የሚፈጸሙ የግዥ አይነቶች ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የጥገና ዕቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ እንዲሁም ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች (ድርጅቶች) መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግዥ ንብ /አስ/ደ/የስራ በሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳዳሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት እስከ 16ተኛዉ ቀን 2፡15 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚሁ እለት 2፡30 ታሽጎ በድጋሚ በዚሁ እለት 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በሎት ስለሚታይ ተጫራቾች ሁሉንም በሎቱ የተገለፁትን ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡
- ከሎቱ ውስጥ አንዱን ያልሞላ አጠቃላይ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ ከፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል 100 ሜትር ገባ ብሎ ከኦክስጅን ማቀነባበሪያ ጎን ይገኛል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 220 0 771 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-ዉድድሩ የሚካሄደዉ ጠቅላላ የሎቱ ድምር ስለሆነ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በሰነዱ ላይ ያሉትን የእቃ ዝርዝሮች በሙሉ መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡
የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

