ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
32

በአብክመ ጤና ቢሮ የዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት እቃዎችንና ህትመቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ  መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጨማሪ አሴት ታከስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾቾ የዳንግላ ሆስፒታል ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት መወዳደር የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ ብር 200 (ሁለት መቶ ) በመክፈል ከገዥ ሩይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር72 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ስሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ዳንግላ ሆስፒታል ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 72 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 72 በ16ኛው ቀን በ4፡30 ይከፈታስ፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ዳንግላ ሆስፒታል ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በሎት (በጠቅላላ ዋጋ) ወይም በነጠላ ዋጋ ሊሆን ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሱ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ቢሮ ቁጥር 72 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058  14  00 574 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here