በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በከ/መ/ል/ጽ/ቤት ስም ለሚያሰራው የኮሪደር የጠጠር መንገድ ስራ ጥራቱን የጠበቀ ጋራጋንቲ እራሱ አምርቶ በሜትር ኪውብይክ በማቅረብ ከቦታው ድረስ ደፍቶና በትኖ የመጠቅጠቅ ስራ የሚሰራ ፤ቦታውም ከሃይስኩል ት/ቤት እስከ ሳቅደብር መገንጠያ ከአስፓልቱ ዳር ለዳር ለሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ማቅረብ የሚችሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና በመንገድ ስራው የስራና የመልካም ስራ አፈፃፀም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንገድ ስራ ኮንስትራክሽን /WWC/ደረጃ7እናከዚያበላይ የሙያፍቃድ ያለው/ያላት
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ ወይም በፉልዱ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን /ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው 1ኛ የወጣውን ውል እስከ ሚወስድ ድረስ 2ኛ የወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሥዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት መጋቢት 07/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን መጋቢት 22/2018 ዓ/ም በተዘጋጀው ሳጥን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አያግደውም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ከቀረበው አጠቃላይ የሥራ መጠን ዋጋ ላይ እስከ 20 በመቶ መቀነስ እና መጨመር ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 118 08 46 /09 35 28 46 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአምባጊዮርስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

