በጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ በበጀት ዓመቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የእህል አቅርቦት፣ ሎት 2 የወጥ ማጣፈጫ፣ ሎት 3 የማገዶ እንጨት፣ ሎት 4 አትክልት ለ6ወር የሚቆይ ተቋሙ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን ጽ/ቤቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የሚያቀርቡ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸወ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል ለግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ የሚሞሉትን አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድረጅት የአሽነፈውን እቃ ጭልጋ ማረሚያ ቤት መጋዝን ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጅዎች ማለትም ዋናውንና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የጭልጋ ወረዳ ማረ/ቤት አስ/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ አስ/ ቡድን መሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ ቀናት ከመጋቢት 07/2018 እስከ መጋቢት መጋቢት 21/2018 ዓ/ም እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርበታል፡፡ የጨረታው ሳጥን መጋቢት 22/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ንብ አስ/ቡድን መሪ መጋቢት 22/2018 ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 07 24 47 /09 18 22 82 96 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡ በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች በጥቅል ዋጋቸው አሽናፊው ይለያል፡፡
የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት

