የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
39

በአፈፃፀም ከሳሽ አቶ እሱባለው ኑሬ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ በቄስ ጌቴ ምህረት መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ጉዳይ የአፈፃፀም ተከሳሽ የተወሰነበትን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት የአፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኙም በምሥራቅ የትዋለ አሳየ፣ በምዕራብ መኮነን ቦጋለ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ እንግዳ ዘለቀ መካከል የሚገኘውን መኖሪያ ቤት ፍ/ቤቱ በመነሻ ዋጋ 1,032,235.38 (አንድ ሚሊዮን ሰላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ከሰላሳ ስምንት ሳንቲም) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም ጨረታው በጋዜጣ ለ30 ቀን እንዲውል በማድረግ ጨረታው ሚያዚያ 06/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 6፡00 ይካሄዳል ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች በዕለቱ ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የሚችሉ ሆኖ ጨረታውን ያሽነፈ ወገን ያሸነፈውን ዋጋ ¼ ኛውን ወዲያውኑ በሐራጅ ባይ ማስያዝ አለበት፡፡

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here