የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ አልባሳት ማለትም ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ፍራሽ እና ትራስ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላችሁ እና በጨረታዉ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ደብረ ማርቆስ በሚገኘው ምሥ/ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት አብማ መስመር ዶ/ር ይልቃል ዓይን ህክምና ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት የስራውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ሞልተዉ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ7ኛው ቀን 9፡00 ላይ ይታሽጋል፡፡ በዚያዉ ቀን 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምሥራቅ ጐጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 34 05 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት

