ቁጥር 13/2018
በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሞጣ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ለሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 የጽ/መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒከስ ግዥ፣ እና ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃ በሎት በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸዉ ተጫራቾች መካከል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-2 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለዉ የጨረታ ሰነድ ከሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሎት 1 ለጽ/መሳሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር)፣ ለሎት 2 ለኤሌክትሮኒከስ ብር 7,000 (ሰባት ሽህ ብር) እና ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃ ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታዉ ላይ የሚወዳደሩበትን የጨረታ አይነትና ሎት በመፃፍ ከሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ለጨረታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሁኖ በ16ኛዉ ቀን እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሞጣ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ የወጣ በሎት በመሆኑ በሚወዳደሩበት ጨረታ ሁሉንም ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 661 02 21 /18 90 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 18 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ቤት

