በደቡብ ወሎ ዞን በሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ በፕላን የተመደቡ ነባር እና አዲስ መንገዶችን ለመስራት የሚያስፈልጉ የግንባታ ማሽነሪዎችን 1ኛ.ግሬደር /moter grader/140 h cat manufactured from 2008 g.c up to now days) ብዛት1፣ 2ኛ. ኤክስካቫተር/excavator with jackhammer breaker/HP=325 and above manufactured from 2008 g.c up to now a days ብዛት 1 ባለትልቅ አካፋ ያለው፣3ኛ.ገልባጭ መኪና (dump trunk/loading up to 16m.cube and above) መጫን የሚችል ጎማቸው አዲስ የሆነ ብዛት 2፣3ኛሮሎ (vibratory Roller) 14 ton and above manufactured from 2008 g.c up to now a days) ብዛት 1 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የማሽነሪዎቹ ሞደል ምርት (ስሪት) ከ2014-2023 እ.ኤ.አ አመት ውስጥ የተመረቱ መሆን አለባቸው፡፡
- በስራ ዘርፉ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑ የስራ ግብር ክፍያ የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ዋናውን እና ኮፒ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ዋናውን እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላውን በነፃ ገበያ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን ሲሞሉ በፖስታው ላይም ሆነ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ ህጋዊ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባችኃል፡፡
- ጨረታው ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ፡፡
- ተጫራቾች የአንድ ማሽነሪ ሙሉ የስራ ወጭ ዋጋ እና የጠቅላላ ማሽነሪ የስራ ወጭ ዋጋ መሙላት ያለባቸው ተወዳዳሪ ተጫራች የሚለየው በሎት (በጠቅላላ ዋጋ ድምር ውጤት) ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሁሉም መስሪያ ማሽነሪያቸው የቴክኒክ ብልሽት (spire part) ለውጦች የነዳጅ ዘይት፣ የማሽነሪ ቅባት፣ የሹፌር (ኦፕሬተር ) እና ማንኛውም ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ወጭዎችን በተጫራች የሚሸፈን ሲሆን ከተጫራች በኩል የሚቀጠሩ ሰራተኞች የስነ ምግባር ችግር የሌለባቸው መሆን አለበት፡፡
- የማሽነሪ ኪራይ የስራ ሰአት የሚቆጠረው ለሚሰሩት የስራ ሰዓት ብቻ ነው ለተፈጥሮ ክስተት ማለትም ዝናብ ሲዘንብ የማሽነሪ ስራ ሰአትየሚቋረጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የስራውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ ደረሰኝ ማረጋገጫ ሲፒኦ ለአጅባር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ቦታ አጅባር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ሲሆን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአጅባር መሪ ማዘጋጃ ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-9 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ኦርጅናላቸው ከነ መጫረቻ ሰነዳቸው በፖስታ አሽገው በፖስታው ጀርባ ላይ የተጫራች ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር እንዲሁም በማህተምና በፊርማ ተረጋግጦ ተሞልቶ ከማወዳደሪያ ማሽን ውስጥ በማስገባት አለባችሁ፤ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ማስገባት ይቻላል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 5፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 14 35 29 42 /03 34 47 02 06 ይደውሉ፡፡
የአጅባር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

