በአፈ/ከሳሽ ኑሪያ ከርሲማ እና በአፈ/ተከሳሽ ሙሀመድ አለማር ጣ/ገብ እነ ሀይባ ከርሲማ መካከል ስላለው የባልና ሚስት ክርክር ጉዳይ፤ በሙሀመድ አለማር ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በምስራቅ እሩቅያ ሰይዳ፣ በምዕራብ አለምወርቅ ገነቱ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ የሽየ መካከል ተዋስኖ በባህር ዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒሊክ ክ/ከተማ ምድረገነት ቀበሌ የሚገኘው 250 ካ/ሜትር የመኖሪያ ቤት ካርታ ቁጥር 13885/1997፣የፋይል ቁጥር 23294 የሆነ በመነሻ ዋጋ 5,047,700.95 (አምስት ሚሊዩን አርባ ሰባት ሽህ ሰባት መቶ ብር ከዘጠና አምስት ሳንቲም ሆኖ የጨረታ ማስታወቂያው ከመጋቢት 7/2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 7/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ ሚያዚያ 10/2018 ዓ.ም ጠዋቱ 3፡00 እስከ 7፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም መጫረት የምትፈልጉ ንብረቱ በሚገኝበት ምድረ ገነት ቀበሌ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

