የፍኖተሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም ሎት1. ጅኤስ ቧንቧና መገጣጠሚያ፣ ሎት2. ኤችዲፒ መገጣጠሚያ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ለሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም በዉሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከ1-5 የተዘረዘሩትን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ::
- የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ይዉላል፡፡ በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ይታሸጋል፤ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይችላሉ::
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማስገባት አይቻልም::
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊዉ ጋር ዉል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያዉ ይመለሳል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 400 (አራት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ::
- አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን የሎት ዕቃዎች ጠ/ዋጋ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለፍኖተ ሰላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ድርጅት አስይዘዉ ዉል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ፍ/ሠ/ከ/ዉ/ፍ/አገ/ ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸዉ ፡፡
- ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ ወይም ሎት በማድረግ ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተጫራቾች ላወጡት ወጪ ድርጅቱ ኃላፊነትን አይወስድም::
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ 058 775 13 87/0075/09 23 42 61 23 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
የፍኖተ ሠላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

