በቋራ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በወረዳው ለሚገኝ ሴ/መስሪያ ቤቶች በ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የወተት ፍየል፣ ሎት 3 የእንቁላል ደሮ እንዲሁም ሎት 4 የውሃ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ለይቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚመለከታቸው ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚፈለገውን እቃ አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊክሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቋራ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና በመሂ 1 የተቆረጠ ጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒ አድርገው በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቋራ ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 መጋቢት 14/2018 እስከ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም 12፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቋራ ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በቀን መጋቢት 29/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቋራ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በቀን መጋቢት 29/2018 ዓ/ም 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸው የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ በቀን መጋቢት 29/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ሎት 2 የወተት ፍየል በቀን መጋቢት 29/2018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል፡፡
- ሎት 3 የእንቁላል ደሮ በቀን መጋቢት 30/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ሎት 4 የውሃ ዕቃ በቀን መጋቢት 30/2018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ቋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስከረብ አለበት፡፡
- እቃውን የምንረከበው በያዝነው የበጀት ልክ ነው፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ወይም ቋራ ወ/ገን/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 058 271 02 69 /00 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

