በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
18

የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለእብናት ወረዳ ግ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክት ዘመናዊ የንጹህ መጠጥ ውሃ የእጅ ውሃ ጉድጉድ ግንባታ 1. ገላ ማጠቢያ ቀበሌ ስዩም ከተማ እና ባርግሃ ጎጥ እንዲሁም 2. ባላርብ ቀበሌ ምሽ ጎጥ እና ኒብላ ጎጥ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሞሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ብቃት ያላቸው የሰው ሃይል፣ የግንባታ መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶችን በሚፈለገው መጠን እና ጥራት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የሰለጠኑበት የስልጠና ሰርተፊኬት ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የአርቲዝያን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. መልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  8. የተቀመጠውን የሥራ ዝርዝር አንብቦ መተግበር የሚችሉ እና ከዚህ በፊት ዘመነዊ የንጹህ መጠጥ ውሃ የእጅ ውሃ ጉድጉድ ግንባታዎችን በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን ሚያረጋግጡ ደብዳቤዎችን ወይም የውል ስምምነቶችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ ድምር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ እ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦጅናል የጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ ደረቅ ቸክ ማቅረብ አይቻለም፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥ እና ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን ቆይቶ በ22 ተኛው ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥ እና ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊው ለስራ በተፈለገበት ወቅት ለ3 ቀናት ተጠብቆ ካልቀረበ በመመሪያው መሰረት መስሪያ ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር በሚሞሉበት ወቅት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ መሆን ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
  14. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 08 የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  15. አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እ/ወ/ግ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  17. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በተጨማሪ ለ21 ቀን ጸንቶ ይቆያል፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 06 06 /218 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here