አፈ/ከሳሽ እንደግ የእቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አስማረ ገረም 3 ራሳቸው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአፈ ተከሳሽ አስማረ ገረም ንብረት የሆነውን በቲሊሊ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ አስማረ ገረም፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ንጉስ ወርቅነህ እንዲሁም በደቡብ ልኬ ዘለቀ መካከል አዋስኖ የሚገኝ 250 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ቤት ግምቱ ብር 1,515,491.98 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ አምስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከዘጠና ስምንት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ከመጋቢት 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ 30 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ ማንኛውም ተጫራች በቦታው ተገኙቶ እንዲጫረት ፤የጨረታ አሸናፊውም ¼ ኛውን በወቅቱ ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባይ በፍ/ቤቱ አካውንት አማራ ባንክ እንዲያስይዝና የጨረታው ውጤትም ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም እንዲገለጽ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት

