በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ለድልድይ እና ኮሪደር ግንባታ የሚውሉ የተለያዩ ማቴሪያሎችን ማለትም ሎት 1. ስሚንቶ፣ ሎት 2. የተለያዩ የግንባታ ብረታ ብረቶች እና ሎት 3. የግንባታ አሽዋና ጠጠር በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች ያለዉን መስፈርት አሟልተዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የእቃው ግዥ መጠን ብር ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ እለት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅት ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ባይገኙም በጽ/ቤቱ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፍቱ መሆኑን እየገለጽን የመክፈቻ ቀኑ ማለትም በ16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ለሎት 1. ብር 20,000፣ ለሎት 2. ብር 20,000 ለሎት 3. ብር 10,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት ድምር ዋጋ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች በመጫረቻ ሰነዱ የተዘረዘረውን ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ ዱርቤቴ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች (አገልግሎቶች) ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ ዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 08 16 /09 74 50 58 99 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

