ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
31

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኘው ለጃናሞራ ወረዳ ሴ/መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ሎት 1. የጃናሞራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በክልል ቀበሌ ምሃሪ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ብሎክ ባለ አራት የመማሪያ ክፍል ግንባታ በመሉ ዋጋ ማስገንባት፣ ሎት 2 የጃናሞራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በዋሰል ቀበሌ ዋስል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አስተዳደር ቢሮ ጥገና ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት፣ ሎት 3. የጃናሞራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመካነ ብርሃን ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚያሰራው አንድ ብሎክ የህፃናት መማሪያ ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት እንዲሁም ሎት4. የጃናሞራ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት በመ/ብርሃ ቀበሌ ከተቋሙ ገቢ ለወረዳው ሰላም አስከባሪ የመመገቢያ እና የምኝታ ክፍሎች ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በተቋሙ የሚሸፈኑ ቆርቆሮ እና ሚስማር ሲሆን ሌሎች ሙሉ አቅርቦቶች በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የህንጻ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በህንጻ ግንባታ ስራ ተቋራጭ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ለተጨማሪ ሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነደቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በእያንዳንዱ ሎት የግንባታው አይነትና ዝርዝር መገለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 15 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ (ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ከመጋቢት 14/2018 ዓም እስክ ሚያዚያ 04/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት መጋቢት 14/2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 04/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 10 ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ 4፡15 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  11. ጨረታውን የምናወዳድረው ከእያንዳንዱ ሎት ድምር ሲሆን ጨረታው ለ40 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  12. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  13. ተጫራቾች ከሚሞሉት ስነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 /24 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here