በድጋሜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
51

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በሎት 1. የጤና ጣቢያው የመለስተኛ ቀዶ ጥገና ክፍል ለማስጨረስ፣ በሎት2. የምርመራ ክፍል ግንባታ ለማስጨረስ፣ ሎት 3. ለፋርማሲ ክፍል ማስፋፊያ ግንባታ ስራ ለማሰራት የእጅ ዋጋ እና ማቴሪያልን ጨምሮ ጥቅል ዋጋ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  4. ሁሉም ተጫራች የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. በከተማ ልማት የግንባታ ምስክር ወረቀት ከደረጃ 7 እና በላይ ያላቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከጤና ጣቢያው ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጠዳ ጤና ጣቢያ በግዥና ፋን አስ/ቡድን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ስዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በ22ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. የስራዉ ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዉድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
  11. በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 058 448 03 33 ደውለው መጠየቅ ወይም ጠዳ ጤና ጣቢያ ፋን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጠዳ ጤና ጣቢያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here