የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. እቴሽነሪ ሎት 2. የደንብ ልብስ፣ ሎት 3. ፈርኒቸር የአገር ውስጥ፣ ሎት 4 የጽዳት እቃ ሎት 5. ህትመት፣ ሎት 6 እና 7 የመኪና ጎማ እነዚህን በዝርዝሩ የተጠቀሱትን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መወዳደር የሚችሉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከለ (ቫት) ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ በሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ሙሉ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር በማስፈር ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማሰያዝ የሚችሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋቸውን ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋጋውን 2 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመጋቢት 14/2018 እስከ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ጃዊ/የመ/ደ/ሆ/ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 29/2018 በ8፡00 ታሽጎ መጋቢት 29/2018 በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝሩን (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኙት ይችላሉ፡፡
- እቃውን ጃ/መ/ደ/ሆስፒታል መካዝን ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተቋሙ ጨረታውን ከጠቅላላ ድምር 20 በመቶ የመቀነሰና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 278 03 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

