የፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ዲሰትሪክት አቶ እንየዉ እሸቴ ቆያቸዉ በፀደይ ባንክ ይልማና ዴንሳ ቅርንጫፍ የተበደሩትን ብድር በዉሉ መሰረት መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ አመላለስ በሚያዧ የተያዙትን በተበዳሪዉ ስም የተመዘገቡ ከዚህ በታች በአዋሳኝ የተገለጹትን ቤቶች በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት 1ኛ. በአቶ እንየዉ እሸቴ ቆያቸዉ ስም የተመዘገበ እና በአዴት ከተማ 04ቀበሌ ልዩ ስሙ ጋፋት የሚገኝ የካርታ ቁጥር ከአገ/118149/15 የሆነ በሰሜን ተመሰገን፣ በደቡብ መንገድ፣ በምሥራቅ ጀማል ሲራጅ እንዲሁም ምዕራብ እንድሪስ ሁሴን የሚዋሰን እና የቦታዉ ስፋት 150 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ግምት ብር 1,786,364.03 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ ስድስት ሽህ ሶስት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከዜሮ ሶስት ሳንቲም ) ይጫረታል፡፡2ኛ. በአቶ እንየዉ እሸቴ ቆያቸዉ ስም የተመዘገበ እና በአዴት ከተማ ቀበሌ 03 ልዩ ስሙ ጤና ጣቢያ የሚገኝ የካርታ ቁጥር ከአገ/114040/14 የሆነ፤ በሰሜን መንገድ፣ በደቡበ 88 ቁጥር ፣ በምሥራቅ አሰፋ ሀይሉእንዲሁም በምዕራብ 94 ቁጥር መካከል የሚገኝ የቦታዉ ስፋት 150 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ግምት ብር 796,549.09 (ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ሽህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ይጫረታል፡፡የሐራጅ ጨረታው ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 ባለዉ ጊዜ ከላይ በተገለጸዉ መነሻ ዋጋ ይጫረታል፡፡ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ፍ/ሰላም ከተማ የሚገኘዉ ፍ/ሰላም ዲስትሪክት ቢሮ ግራዉንድ ላይ ነው፡፡ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋዉን 1/4 በፀደይ ባንክ ማንኛዉም ቅርንጫፍ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘዉ መቅረብ አለባቸዉ፡፡ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የሚጫረተዉ ሰዉ ዉክልና እና የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ይዞ መቅረብ አለበት፡ለመንግስት የሚከፈል ማንኛዉም ግብር ቫትን ጨምሮ እንዲሁምከመንግስት የሚጠየቅ የሊዝም ሆነ ከቦታዉና ቤቱ ዝዉዉር ጋር የተያያዘ ማንኛዉም ክፍያ በተጫራች (በገዥ) የሚሸፈን ይሆናል::የጨረታው አሸናፊ ጨረታዉን ባሸነፈ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉውን ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅና ቤቱን መረከብ ይኖርበታል:: በ15 ቀን ዉስጥ ሙሉ ገንዘቡ ካልተከፈለ የተያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ
ሆኖ ሐራጁ እንደገና ይወጣል::ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታዉ አይገደድም፡፡
ፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ዲስትሪክት

