0
21

በአብክመ በምስ/ጎ/አስ/ዞን በእናርጅ እና/ወረዳ የደብረ ወርቅ ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የፋርማሲ ክፍል የአልሙኒየም (APTS) የግንባታ  የአገልግሎትና የእቃ አቅርቦት ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁት መሰረት  ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
  3. በግንባታ ዘርፍ GC ሰራዎች ደረጃ 9 እና በላይ የሆኑ ተቋራጮች የግንባታ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው
  4. የግዥ መጠኑ ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በደ/ወቅ ጤና ጣቢያ ግዥ አስ/ፋ/ን ቡድን ቢሮ ቁጥር 17 በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጠቅላላ ዋጋ5በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ  ወይም የባንክ ጋራንቲከጨረታ መዝጊያ በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን ባማስፈር በታሸገ ፖስታ ባማድረግ ሰነዱን ለማስገባት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 17 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ21 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ2ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00  ይከፈታል እለቱ የበዓላት ቀን ወይም  ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00   ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዥ በአሸነፈበት የእቃውን (የአገልግሎቱን) ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር17 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 663 0316 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የደ/ወርቅ ጤና ጣቢያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here