ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
31

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና የልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርትና፣ በጤና፣ በመሠረታዊ ሙያ ክህሎትና ስልጠና እና ስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ የማድረግ ተልዕኮን አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሃገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበበሩ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በመተባበር ተግባራዊ ለሚያደርገው ኘሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ላፕ ቶፕ እና የስልክ ቀፎ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 412 ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) ከላይ የተጠቀሱ ነጥቦችን መሠረት በማድረግ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በደቡብ ወሎ እና አካባቢው ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 405 ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ላይ ይታሸጋል፣ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 402 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 112 4834 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here