ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን  ኃ.የተ. ሎት1. ሰርገኛ ጤፍ ሰብል ሽያጭ ብዛት ሶስት ሺህ ኩ/ል ባ/ዳር ከተማ መጋዝን የሚገኘውን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ  ማቅረቢያው ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማየያዝ አለባቸው፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00  ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30  ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ቅዳሜ ለዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው ተወዳዳሪዎች ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. አሸናፊው ያሸነፈውን ሰብል በፍትህ ውል ከተመረመረ ለውል ምርመራ (ምዝገባ) ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል ወይም ይሸፍናል፡፡ ሰብሉን ለማንሳት የሚያስፈልጉ ማንኛውም የወዛደር ማስጫኛ እና የትራንስፖርት ወጭዎችን አሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  12. ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዝን የሚገኝ ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሞላት አለበት፡፡ ከሎቶች ውስጥ መጠኑን ቀንሶ መሙላት አይቻልም፡፡
  13. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  14. ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ በህ/ስ/ማ/ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 18 08 26 28 /09 11 59 05 34 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here