የደቡብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ለደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ አገልግሎት የሚውሉ የሰፖርት ትጥቆችን በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚያቀርቡ፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማስረጃዉን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚቀርበው ፎቶ ኮፒ የሚነበብ እና በተናጠል መሆን አለበት፡፡
- የሚፈለጉ የስፖርት ትጥቆችን ሰነድ እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫረቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደርበት ጥቅል ዋጋ ድምር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መግዛት አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ 1 በመቁረጥ ደረሰኙን አብረው አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በደ/ጎ/ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት በአሸነፈበት የዋጋ ድምር 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 07 53 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

