የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የኤሌክትሮኒክስ፣ የካሜራ እና የፋይል መደርደሪያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የተጠቀሰውን ዕቃ ማቅረብ የሚችሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸዉ አቅራቢዎች ሁሉም በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር የኤሌክትሮኒክስ ግዥ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ብቻ የካሜራ ግዥ ብር 15,000(አስራ አምስት ሺህ ብር) እና የፋይል መደርደሪያ ግዥ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) የሚወዳደሩ ከሆነ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ወይም (ቢድ ቦንድ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ ገቢዎች ቢሮ ባሕር ዳር ቁጥር 313 የቢሮ ህንፃ ከላይ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) የካሜራ እና የፋይል መደርደሪያ ግዥ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ ማስገባት የሚችሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡ ሁኖም 16ኛዉ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
- ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻችን፡- ባሕር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ግብርና ምርምር ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ

