ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
23

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ ከአሰሪና ሰራተኛ ባለስልጣን ወደ ስራና ክህሎት ቢሮ ለተዋሃዱ ሀላፊና ባለሙያዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ፕሪንተር ቀለም እና ፎቶ ኮፒ ቀለም፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4. የመኪና ጎማ፣ ሎት 5. የጽ/እቃዎች እንዲሁም ሎት 6. የሰራተኛ ደህንነት መቆጣጠሪያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታ ሰነዱ መሠረት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊና በዘርፉ የተሰማሩ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዥው ከብር 200,000 እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር G001 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ ለሎት ብር 5,000፣ ለሎት 2. ብር 5000.00፣ ለሎት 3 ብር 5,000፣ ለሎት 4 ብር 5,000 ብር ለሎት 5 ብር 5,000 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በቢሮ የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛዉ ቀን ማለትም ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኘዉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ዉስጥ ወይም ሁለተኛ ፎቅ ሚኒ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ አስራ ስድስተኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ቢሮዉ ጨረታዉን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  9. ቢሮው ላሰራር ይመቸው ዘንድ ውድድሩ ወይም ጨረታውን በጥቅል የሚያወዳድር በመሆኑ ተወዳዳሪዎች ወይም ተጫራቾች የሁሉንም እቃ ሞልታችሁ እንድታቀርቡ እናሳስባለን፡፡
  10. ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 53 97 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here