ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን (EOC-DICAC) እ.ኤ.አ. በ1972 የቤተክርስቲያኗ የልማት ዘርፍ ሆኖ የተቋቋመና የተመዘገበ የኢትዮጵያ አገር በቀል ተራድኦ ድርጅት ነው፡፡ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ኮሚሽኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የተለያዩ የልማትና ሰብዓዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ባለው የስራ እንቅስቃሴዎች መካከል በአማራ ክልል በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ የሚገኝ “የሴቶችን መብትና ጽናትን ማጠናከር” የተሰኘ ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ ለመዋለ ህፃናት ተማሪዎች የሚሆን መጸዳጃ ቤት ለመገንባት ከደረጃ BC/GC 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ከሚመለከተው አካል መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ወቅታዊ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተዛማጅነት ያለው የሥራ ልምድ እና የቴክኒክ ባለሙያዎች የታደሰ የሙያ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  4. ለሥራው የሚያስፈልጉ የግንባታ መሣሪያዎች እና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የፋይናንስ አቅም መግለጫ ወይም የብድር አገልግሎት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
  5. የተመረመረ የፋይናንስ መግለጫ (Audited financial statement) እና ከቀድሞ ደንበኞች ጋር መልካም ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  6. ፍላጎትና ብቃት ያላቸው ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሰቆጣ ከተማ በሚገኘው የኮሚሽኑ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ወይም አ/አበባ 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ ሰነዱን ብር 400 (አራት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ከተፈቀደ ባንክ የተረጋገጠ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
  8. የፋይናንስ ሰነዶቹ ዋናውና ኮፒው እና የቴክኒክ ማስረጃዎች (ዋናው ብቻ) በተለያዩ ኤንቨሎፖች መቅረብ አለባቸው፡፡
  9. በሁሉም የዋናውና የኮፒው ሰነድ ገጾች ላይ ማህተም እና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
  10. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ90 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  11. ጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋል፡፡ በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 09 14 14 64 90 ወይም 09 11 24 02 18 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

EOC-DICAC ሰቆጣ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here