በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
14

በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ  ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም  በጀት አመት ለመ/ቤቱ  አገልግሎት የሚዉሉ  ሎት 1. የጽህፈት  መሳሪያ፣  ሎት 2. የቧንቧ ውኃ እቃ፣ ሎት 3. የኤሌክትሪክ እቃ፣ ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ  እቃ፣ ሎት 5. ፈርኒቸር፣  ሎት 6. ጀኔሬተር እና ሎት 7. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን  ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች  የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ግዥው ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው  ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ እና የሚጠገኑ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም መግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ  በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም (ሲፒኦ) ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሪው  ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በስራ ሰዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከመጋቢት 21/2018 እስከ ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም ሚያዚያ 06/2018  ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በወቅቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ሁሉ ተገዥ ይሆናሉ፡፡  ጨረታው በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል እቃ ዋጋ ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በነጠላ ዋጋ አሸናፊ መለየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንዳር ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን መተማ ጠቅላላ  ሆስፒታል  ባለው ንብረት መጋዘን በዝርዝር ማስረከብ የሚችል፡፡
  10. አሸናፊው እቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጂ ስርዝ /ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
  11. መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ እቃ አቅርቦት 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. ስለ ጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 03 54 /058 331 01 75 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የመተማ  ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here