ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
13

በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት በአስተዳደር ግቢ ውስጥ በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚሰጥ G+3 የቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡፡

  • በግንባታው የሚሳተፉ የተቋራጮች ደረጃ GC&BC -5 በላይ የሆኑ፡፡
  • ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) እና የግንባታ ፈቃድ በዘርፍ ለመሰማራታቸው በወቅቱ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  • ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) ብቻ በሲፒኦ በባንክ ፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ስም እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ የሚያሲይዙ ከሆነ ለመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 1 በገቢ ደረሰኝ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በፖስታው አብሮ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታው የሚገመገመው በመደበኛው የክልል የግዥ መመሪያ መሰረት ሲሆን የጨረታ መመሪያ እና አጠቃላይ የውል ሁኔታም በተቀመጠው የአነስተኛ ግንባታ (ህንጻ) አጠቃላይ የውል ሁኔታ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  • በጥቃቅን የተደራጁ ተወዳዳሪዎች የሚገመገሙት ልዩ ድጋፍ ሳይደረግ እንደ ማንኛውም ሌሎች ተጫራቾች እኩል ስለሚገመገሙ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በተጠየቀው አግባብ አዘጋጅተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • በጨረታው አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በጨረታ ሰነዱ የቀረበውን የቴክኒክ መስፈርት መሰረት ተገምግመው የሚያልፉት ተጫራቾች መካከል በዋጋ ተነፃፅሮ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ነው፡፡
  • ተጫራቾች የቴክኒካል ማወዳደሪያ መስፈርቶችን ከጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት አሟልተው ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሻል ዋጋ የሞሉበት የማወዳደሪያ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ  በማድረግ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ኢንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የቴክኒካል ማወዳደሪያ መስፈርቶችን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በቀረበው የዋጋ መሙያ (ቢል ኦፍ ኳንቲቲ) ቅጽ መሰረት የአንዱን የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ፣ስምና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አሸናፊው ድርጅት ከተለየ በኋላ ለግንባታ ስራው የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና 10 በመቶ እና መ/ቤቱ ለሚከፍለው 30 በመቶ ቅድመ ክፍያ ዋስትና በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ጋራንቲ (ሲፒኦ) ከህጋዊ ባንክ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) በፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት አስከ 21ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከሚዘጋበት ከ3፡30 በኋላ የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የማይኖረው ሲሆን ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 3፡45 ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ማንኛውም ተጫራች ባቀረበው የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻል ማድረግ እና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆኑ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  • የጨረታ መገምገሚያ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተ ጊዜ አንስቶ ለ40 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ግምገማው ከተቀመጠው ጊዜ በላይ የሚፈጅ ከሆነ ተቋሙ ዕጩ ተጫራቾችን የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበትን ተጨማሪ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
  • አሸናፊው እንደተለየ እና የቅሬታ ማስተናገጃ ጊዜው በተጠናቀቀ በአምስት ቀን ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል የሚያዝ ይሆናል፡፡ የግንባታ ቦታ ርክክቡም ውል በተያዘ በአምስት ቀናት ውስጥ ይፈጸማል፡፡
  • የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም የቦታ ርክክብ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ከተቋሙ ጋር በፍትህ በሚፀድቅ የውል ቀን ይሆናል፡፡
  • የጨረታ ሠነድ የመሸጫ ዋጋ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ ነው፡፡
  • ርክክቡ የሚፈፀመዉ ስራዉ በሙያተኛ ተረጋግጦ ነዉ፡፡
  • ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች ያወጡትን ወጭ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ ይሆናል፡፡
  • በማስታወቂያው ያልተገለጹ ነገሮች ካሉ በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  • ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ደዉለዉ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here