በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከተያዘዉ ከመሰረተ ልማት ከውጭ መደብ 6324 መሰረት በከተማችን ዉስጥ አሰፓልት እየተሰራ ስለሆነ የመንገድ ዳር ኮሪደር ለማሰራት በደረጃ 5 ከዚያን በላይ ያላቸዉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሠነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሰራዉ ኮሪደር ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የኮሪደሩ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሠነድ የሚሸጥበት ቦታ ደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ነው፡፡
- ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን ሠነድ መመለስ የሚችሉት ጋዜጣው ከወጣበት እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ15ኛው ቀን 11፡30 የጨረታ ሳጥኑ የታሽጋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾችም ሆነ ወኪሎቻቸው ባይገኙም እንኳን ጨረታው በእለቱ ደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- የተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ተነባቢ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የሚሰራዉ ቦታ ከወ/ሮ ትዛለች ተመስጌን ቤት እስከ ጊዜ ወፍጮ ቤት ድረስ ያለውን ኮሪደር ነው፡፡
- በኮሪደር ስራ መልካም አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ውድድሩ በሎት በጥቅል ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ቦታው ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ከደብረ ማርቆስ ከተማ በምዕራብ አቅጣጫ 42 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለጋችሁ በከተማው መሪ ማዘጋጃ ቤት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 250 02 30 /668 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

