በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ እቃ ለመግዛት የወጣ ግልጽ ጨረታ፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የታደሠ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ (ቲን) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለእቃው ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 102 ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በኦርጅናሉ የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመግዛት ሚያዝያ 3/2018 ዓ.ም 6፡30 ታሽጎ ሚያዝያ 5/2018 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታው ከሚቀርቡ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 2 በመቶ በባንክ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ዋጋ የሚሞላውና ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፡፡
- በጨረታው የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የሆነ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ተጫራቾች በወቅቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ እቃውን ማስረከብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 058 218 14 24 /058 218 06 44 /058 218 00 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት

